በተጭባጭ እውቀት ህሊናን አርቅቆ፣
በልእለ ምጥቀት በበሰለ እይታ
ያለፈን ፈትሾ ገምግሞ በእርጋታ፣
መጪውን መተንበይ በጥበብ አሻግሮ
የሂወት ልምድ ይሻል የተኖረ ኑሮ፤
ቀመር አበጅቶ ደንግጎ ህግጋት
በፍቅር የመኖር የመስከን የመርጋት፣
ነግርን መከወን በጥልቅ አገናዝቦ
በስሜት ላይ መንገስ አራስን ገድቦ፣እሚያስረዳ ጠቢብ ሲቸረን ፈጣሪ፣
የሰም እና ወርቁ የአለም ቋንቋ ቅኔ
ጭጋጉ ተገፎ ይገባናል ያኔ።

እጅግ ጥሩ አገላለፅ
ምላሽ ይስጡሰርዝአመሰኛለሁ ❤
ሰርዝ